” ፍትህ የማናገኝ ከሆነ ለኢትዮጲያ እግርኳስ ፍትህ ስንል እስከ አለም አቀፉ የግልግል ፍ/ቤት እናቀናለን

 

👉” ፍትህ የማናገኝ ከሆነ ለኢትዮጲያ እግርኳስ ፍትህ ስንል እስከ አለም አቀፉ የግልግል ፍ/ቤት እናቀናለን”
አቶ ዳዊት ትርፉ  /የአ/አ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ም/ል ሃላፊ/


” ክለቡ ከተመሠረተ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ቢያድግም እግርኳሳዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንድንወርድ ተደርገናል”ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ከሰሰ።

የክለቡ አመራሮች በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጡት መግለጫ እንደተገለጸው እግርኳሳዊ ባልሆነ መንገድ በመውረዳችንና ይህን አቅጣጫ ለማስቀየስ አዲስ አበባ ለቋል የሚል በሬ ወለደ የሚለው መረጃ አሳዝኗል” ሲሉ ተናግረዋል። የከተማዋ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ም/ል ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እንደተናገሩት “የመጨረሻ ጨዋታ ከመካሄዱ ከሁለት ቀን በፊት ጨዋታው በደንብ ይታይልን በሚል ለሊግ ኩባንያውና ለፌዴሬሽኑ አሳውቀናል። ክለባችን እንዲወርድ መታሰቡንም ሰምተናል ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረንም ጨዋታ ብናሸንፍ አንድም ሰው በህይወት አይተርፍም ለአዲስ አበባ ልትለቁ በጠረጴዛ ላይ ተወያይታችሁ ነው የመጣችሁት ተብለን ዛቻ ሲሰጠንም ነበር የባህርዳር የወልቂጤና የፋሲል ከነማ ደጋፊና አመራሮች ዛቻ ሲገርመን ነበር ስም አልጠቅስም አታግባና አታሸንፉና ደቡብ አፍሪካ ይናፍቅሃል የሚሉ ደጋፊና አመራር ማየት ያሳዝናል ” ሲሉ የሂደቱን ጅማሮ ገልጸዋል።

” ከሲዳማ ቡና ጋር ስንጫወት በትሪቩን በኩል የነበረ ረዳት ዳኛ የድሬዳዋ ዳኛ ነው ከድሬዳዋ ጋር ላለመውረድ እየታገልን ዳኛው መመደቡ ገርሞናል ከጨዋታ ውጪ ያልነበሩ ኳሶችን ከጨዋታ ውጪ ነው ብሎ ሲያስቆም ነበር እኛ ላይ የተገኘው ግብም ልክ አይደለም ከዳኛ ምደባ ጀምሮ ጫና ነበረብን” ያሉት አቶ ዳዊት “የአዲስ አበባ ከተማ መደራደር ቢፈልግ ከክለቦች ጋር መደራደር እንችል ነበር ይህን ለማድረግ ግን አናስብም ለወደፊት አይታሰብም በፌዴሬሽኑ 33 ድምጽ ያላቸው ክለቦች አዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው ይህን ለሀገሩ ስፖርት ትልቅ ድርሻ ያበረከተው ከተማ ለመጣል የተደረገው ሂደት አሳዝኖናል” ሲሉ ተናግረዋል።

” አዳማ ከድሬዳዋ አቻ ነው የሚወጡት ተብሎ ተነግሮናል ይህን መረጃ ከሲዳማ ቡና ጋር አቻ እንደወጣን ሰማን ሁሉ ስራ አስቀድሞ ተሰርቷል።ለበርካታ ሰዎች አመራሮች ለቅርብ ጓደኞቼ ስናገር አላመኑኝም እንደኔ ጨዋታው አቻ ባያልቅ ዜናውም ዜና ባልሆነ… ነገር ግን እስከመጨረሻ ሰአት ድረስ የራሳችንን ዕድል የመወሰን መብታችንን ባለመጠቀማችን ተጎድተናል” ሲሉ አስረድተዋል።

ም/ል የቢሮ ሃላፊው እንደተናገሩት ” ከፌዴሬሽኑና ከአወዳዳሪ አካል ፍትህ እንፈልጋለን.. ያ የማይሆን ከሆነ
በርግጠኝነት ለኢትዮጲያ እግርኳስ ፍትህ ስንል እስከ አለም አቀፉ የግልግል ፍ/ቤት እናቀናለን…. በኛ ግምገማ በርካታ ክለቦች በጨዋታ ማጭበርበሩ ውስጥ ተሳታፊ ናቸው የሀዋሳ ከተማና አዳማ ከተማ ጨዋታም የመጨረሻ ጨዋታ የውጤት ማጭበርበር ላይ ተሳታፊ ናቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ ተናግረናል።

” በ30ኛው ሳምንት ጨዋታ ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት ተገቢ ያልነበረና የራሳችንን ዕድል በራሳችን እንዳንወስን አድርጎናል ዳኛው ዕድለኛ እንደሆነ የማስበው ስለዚህ ስህተት ያወራ ስላልነበር ነው ይህንን ክስተትንም በክስ አሲይዘናል” ሲሉ አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለቋል የተባለው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው በበኩሉ” ቋሚም ተቀያሪም ተጨዋች የመምረጥ መብቱ የአሰልጣኞች ነው የተቀጣ የታመመ በአቋም የወረደ በሚል ቋሚና ተቀያሪ ተጨዋቾችን መርጠናል በፍጹም አለቀቅንም.. መሬት የማበረታቻ ሽልማት በአምስት እጥፍ አድጎልን አምስት ባለሀብቶች ሊሸልሙን ቃል ገብተውልን እንዴት ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንለቃለን..?” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የክለቡ ቡድን መሪ አቶ መሠረት ” በተደረገው ሸፍጥ አዝኛለሁ ተጨዋቾቹ ያሳዩትን ሀዘን አሁን ድረስ አልወጣልኝም…ከጨዋታው በፊት በነበረ የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ የኛና የቅ/ጊዮርጊስ ጨዋታ ዳኛ ዶክተር ሃ/የሱስ ባዘዘው መሆኑን ሲነገር የፋሲል ከነማና የድሬዳዋ ከተማ ቡድን መሪዎች የጊዮርጊስና የአዲስ አበባ ከተማ ዳኛ መቀየር አለበት ሲሉ ገረመኝ ለምን እንዳሉ አልገባኝም በአጠቃላይ በሂደቱ ተከፍቻለሁ ድሬዳዋ ሲያገባ የጨፈሩ ደጋፊዎች ሳይሆኑ ፍትሃዊ ባልሆነ ድርጊት ያዘኑ ንጹህ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አጽናንተውናል…የባህርዳር ከተማ ነዋሪን ለነበረው አብሮነት እናመሰግናለን ሁለቱ የወረዱትን ክለቦች ጨምሮ ወደ 10 የሚጠጉ ክለብ ቡድን መሪዎች አይዟችሁ ከናንተ ጎን ነን ብለውናል ያገዙንን እናመሰግናለን” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በ30ኛ ሳምንት የሀዋሳ ከተማና የአዳማ ከተማ፣ የድሬዳዋ ከተማ ና የፋሲል ከነማ እንዲሁም የቅ/ጊዮርጊስና የአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ የሚመለከታቸውን አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ዳኞችና ኮሚሽነሮችን ለመጪው ረበዕ በተለያየ ሰአት ለማናገር ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።

0 Comments