!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሐሙስ ግንቦት 11 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በ24ኛ ሳምንት የተደረጉ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ውጤት በማፅደቅ እንዲሁም የዲሲፕሊን ሪፖርትም ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።
በተጫዋቾች አላዛር ማርቆስ ፣ ተስፋዬ መላኩ ፣ አቡበከር ናስር ፣ ጸጋዬ አበራ ፣ ፉዓድ ፈረጃ እና ዮሴፍ ዮሀንስ በተለያዩ የክለባቸው ጨዋታዎች አምስተኛ ቢጫ ካርድ በማየታቸው በቀጣይ 1 ጨዋታ እንዲታገዱና 1500 ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም ዊሊያም ሰለሞን አስረኛ ቢጫ ካርድ በመመልከቱ ለፈፀመው ጥፋት ሁለት ጨዋታ እንዲታገድ እና 2000 ብር እንዲከፍል ውሳኔ ተላልፏል።
በክለቦች አርባምንጭ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ሰበታ ከተማ የክለባቸው የተለያዩ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ቢጫ ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በመመሪያው መሰረት 5000 ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን የጨዋታ አመራሮች በተደጋጋሚ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበትና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት አጥፍተው ክለቡ መቀጣቱን በዚህም ደጋፊዎቹ ከድርጊታቸው አለመማራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የ75000 ብር ቅጣት ተጥሎበታል ሲል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያወጣው መረጃ ያመላክታል።
0 Comments
HABESHAWI SPORT