።
መከላከያዎች በ24ኛው ሳምንት በፋሲል ከነማ በተረቱበት ጨዋታ የነበረውን ምርጥ 11 ሙሉ ለመሉ ይዘው ሲገቡ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ነጥብ በታሩበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦቶችን በማድረግ በዳንኤል ደምሴ ፤ ዳንኤል ኃይሉ እና ሙኽዲን ሙሳ ምትክ አቤል አሰበ ፤ ሱራፌል ጌታቸውን እና ጋዲሳ መብራቴን አሰልፈዋል ።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ መከላከያ የሜዳ ክፍል ለመድረስ በሚያደርጉት ጥረት መከላከያዎች የሚያቋርጡትን ኳስ በፈጣን ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በማድረስ ጥቃቶችን ለማድረስ ሞክረዋል ።
ገና በሁለተኛው ደቂቃ ላይ ተሾመ በላቸው በሳጥኑ የቀኝ አቅጣጫ ላይ ሆኖ ወደ ግብ የመታው ሙከራ የግቡን ቋሚ ለትሞ ተመለሰ እንጂ መከላከያዎች ገና በጊዜ መሪ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ነበር ።
በድሬዳዋ ከተማ በኩል የነበረው ቀዳሚ የግብ ሙከራ 11ኛ ደቂቃ ላይ የተመዘገበ ሲሆን መሀመድ አብዱለጢፍ ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ ጋዲሳ መብራቴ በግንባር ገጭቶ ወደ ግብ ሞክሮ በግብ ጠባቂው ፍሬው ሰለሞን መልሶታል ።
የመከላከያዎች ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ ቶሎ ቶሎ ወደ ድሬዳዋ ከተማ የግብ ክልል ለመድረስ ቢያስችላቸውም ፍሬው ጌታሁንን የፈተነ የግብ ሙከራ ለማድርግ አልቻሉም ነበር ።
በ25ኛው ደቂቃ ላይ ተሾመ በቀኝ መስመር የድሬዳዋ ተጫዋቾች አልፎ የሄደውን ኳስ አዲሱ አቱላ አግኝቶ ወደ ግብ ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል ።
ከውሀ እረፍት መልስ ቀድሞ ከነበረው ቀዝቀዝ ብሎ በቀጠለው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ ጥረቶችን ቢያደርጉም በ32ኛው ደቂቃ ላይ ክሌመንት ቦዬ በሰራው ስህተት የተገኘውን ኳስ ብሩክ ቃልቦሬ አግኝቶ ወደ ግብ ሞክሮ በቀላሉ ከተያዘበት ውጪ ይህ ነው ሊባል የሚችል የግብ ዕድል መፍጠር ሳይችሉ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል ።
ሁለተኛው አጋማሽን ድሬዳዋ ከተማዎች በፈጣን ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በመድረስ ጀመሩ ሲሆን ይህ እንቅስቃሴያቸው ብዙም መቆይት አልቻለም ነበር ። አብዛኛውን የሁለተኛው አጋማሽ መከላከያዎች በድሬዳዋ ከተማ ላይ ብልጫ ወስደው ያሳለፉት ሲሆን በኳስ ቁጥጥሩ እና ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ የተሻሉ ነበሩ ።
በ46ኛው ደቂቃ ላይ ከሰሞኑ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ሄኖክ አየለ ከአብዱራህማን ሙባረክ የደረሰውን ኳስ በሳጥን ውሰጥ ሆኖ ወደ ግብ ሞክሮ በክሌመንት ቦዬ ሲመልስበት ከአንድ ደቂቃ በኋላም አብዱራህማን ሙባረክ ከቀኝ መስመር ተነስቶ ወደ ሳጥን ይዞ ገብቶ ለመቀነስ ያደረገውን ሙከራ በመከላከያ ተጫዋቾች ተመልሷል ።
መከላከያዎች ምንም እንኳን ከፍተኛ ብልጫ ወስድው የድሬዳዋ ከተማ የኋላ መስመር ተጫዋቾች ለመፈተን ቢጥሩም ጠንከር ያለ የግብ ሙከራን ማድረግ የቻለ ተጫዋች ማግኘት አልቻሉም ነበር ።
ደቂቃዎች ሲገፉ እየተቀዛቀዘ የቀጠለው ጨዋታ በሁለቱም በኩል ግብ ጠባቂዎቹን የፈተነ የግብ ሙከራ ሳይደረግ ፍፃሜውን አግኝቷል ።
ውጤቱን ተከትሎ መከላከያ ነጥቡን 31 በማድረስ ወደ 8ኛ ከፍ ሲል ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ በ29 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።
0 Comments
HABESHAWI SPORT