በ23ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ፋሲል ከተማን ከባህርዳር ከተማ አገናኝቶ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በተካሄደው እና በርካታ ክስተቶችን ባስተናገደው ጨዋታ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ፍቃዱ አለሙ ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ አፄዎቹ ማሸነፍ ችለዋል ።

በ23ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ፋሲል ከተማን ከባህርዳር ከተማ አገናኝቶ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በተካሄደው እና በርካታ ክስተቶችን ባስተናገደው ጨዋታ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ፍቃዱ አለሙ ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ አፄዎቹ ማሸነፍ ችለዋል ። ፋሲል ከተማ በ23ኛው ሳምንት ሲዳማ ቡናን በረቱበት ጨወላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦችን በማድረግ ከድር ኩሊባሊ ፤ አምሳሉ ጥላሁን እና ይሁን እንደሻውን በአስቻለው ታመነ ፤ ሰኢድ ሀሰን እና ሀብታሙ ተከስተ ምችክ ሲያሰልፉ በባህርዳር ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከወላይታ ድቻ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 በተመሳሳይ ሶስት ለውጦችን በማድረግ ፉአድ ፈረጃ ፤ ፍቅረሚካኤል አለሙን እና ተመስገን ደረሰን በአለልኝ አዘነ ፤ በረከት ጥጋቡ እና አደማ አባስ ምትክ አሰልፈዋል ። በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ብርቱ ሊባል የሚችል የሜዳ ላይ ፉክክር የተደረገ ሲሆን በፋሲል ከተማ በኩል በጥሩ የኳስ ቅብብል ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ይዘው የሚሄዱት ኳስ በጣና ሞገዶቹ የኋላ መስመር ተጫዋቾች ይበላሽባቸው የነበረ ሲሆን በባህርዳር ከተማ በኩል በተለይም በፈጣን ሽግግር ወደ ፊት መድረስ ቢችሉም የግብ ዕድሎችን በመፍጠሩ ረገድ ደካማ ነበሩ ። ለደቂቃዎች በግብ ሙከራ ያልታጀበው ጨዋታ በ25ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ለግብ የቀረብ የመጀመሪያ አጋጣሚን ያስመለከተን ። አሊ ሱሌማን ከፍፁም አለሙ በሳጥኑ የቀኝ አቅጣጫ ሆኖ የደረሰውን ግሩም ኳስ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ። በቀጣይ ደቂቃዎች ላይ አፄዎቹ በተከታታይ ሁለት የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችለው ነበር ። በ30ኛው ደቂቃ ላይ ኦኪኪ አፎላቢ ከርቀት የቅጣት ምት ወደ ግብ የላከው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል ። ከደቂቃዎች በኋላም በረከት ደስታ ከሱራፋል ዳኛቸው የደረሰውን ኳስ በጠንካራ ምት ወደ ግብ ቢልከውም ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑሪ አድኖታል ። የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ባህርዳር ከተማዎች ወሳኝ የሆነወሰ ተጫዋቻቸው ፍፁም አለሙ በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቶባቸዋል ።

0 Comments